ለቡ ድሮ እና ዘንድሮ፥ | በእለፋቸው ሞሲሳ

0
391

lebuእድሜየን ሲሶ የኖርኩት ለቡ በምትባል በደቡብ አዲስአበባ በምትገኝኝ ቀበሌ ነው::….ድሮ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ነበር የምትባለው ….አሁን ለቁጥር ወግ በቅታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምንትስ ቀበሌ ዜሮ አንድ ተብላለች:: ለቡ ድሮ ድሮ…ሁርቡ የሚባል የክረምት ጀግና ወንዝ እየተገማሸረ ነዋሪውን የሚያሸብርባት….ጎረምሶች የወንዙን ፉከራ ከመጤፍ ሳይቆጥሩ እየዘለሉ ገብተው እወንዙ ዳር ሳር ሲግጥ ሳት ብሎት ገብቶ በ አለልቱ እግሮቹ የተተበተበ ወይፈን የሚታደጉባት …. የለቡ እና የማዶ ልጆች ክረምቱን ሙሉ እና በበጋው ቅዳሜ እና እሁድን ጠብቀው እግር ኩዋስ የሚጫወቱበት ሰፊ ሜዳ የያዘች….ጉርምስናን የተሻገሩት ህዳር ሃና እና ጥምቀትን እየጠበቁ ተሻግሮ ካሉት ገላን እና መኒሳ ቀበሌዎች ከሚመጡ ጎልማሶች ጋር የፈረስ ጉግስ ውድድር የሚያደርጉባት….

ከመሃል ከተማ ልጆች በክረምት ለበዓል የሚበራ ለራሳቸውም …የሚሸጥም ችቦ በነፃነት ለቅመው “ገጠር ሄደን መጣን!” ብለው ጉዋደኞቻቸውን የሚያስቀኑባት… በማገዶ ሽያጭ የሚተዳደሩ የጨርቆስ እና ቄራ አካባቢ እናቶች ከቀበሌው የሚገዙትን እንጨት እና ቅጠል ተሸክመው መሬት ለመንካት ስንዝር እስኪቀራቸው አጎንብሰው በአንዲት ጨፈቃ እርዳታ የሚጉዋዙበትን አንጀት የሚበላ ትዕይንት የምታይበት …በፀደይ ወቅት ለማየት የሚያሳሳ የጤፍ ቡቃያ የሚሰራው ማዕበል ነፍስን ወሰድ የሚያደርግባት…ነዋሪዎች እንደይዞታቸው መጠን አርሰው…ዘርተው…አጭደው ከጎተራ የሚያስገቡባት….የሚበቃቸው እህላቸውን ሽጠው….የማይበቃቸው ጎን ለጎን ከከብት አዛባ እና ከጭቃ የሚሰሩትን አክንባሎ “ቆሼ” እየተባለ ወደሚጠራው አየርጤና አካባቢ ያለ ገበያ ወስደው ሽጠው….

…. ከከብቶች ግጦሽ የተረፈ ስንበሌጥ እና ባለሚ (የሱ ሳር ሽታ እስካሁን ልቤን በሃሴት ይሰውራታል) አጭደው ቄራ ወስደው ሽጠው….ጋዝ …ሳሙና…እና መሰል ሸቀጦችን እንዳቅማቸው ሸምተው የሚገቡባት የገጠር ቀበሌ ነበረች:: በአብዛኛው ኦሮሞዎች የሆኑ ነዋሪዎችዋ ….ከወሎዬዎች…ጎንደሬዎች…አንድ እድር ገብተው….አንድ ፅዋ ጠጥተው….ከአንድ ማዕድ ቆርሰው…. በእሳት የተያያዘ ጎጆን አብረው አትርፈው ….በሰላም የሚኖሩባት የገጠር ቀበሌ ነበረች:: ይሄ የሕይወት ዑደት ባይሻሻል ሳይብስበት ….ሳይደፈርስ እየዞረ መጥቶአል… ለዘመናት! Read More

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here