ተደጋጋሚጭፍጨፋዎች እንዲቆሙ አስጨፍጫፊዎችመወገድአለባቸው እኛምኦሮሞዎችነን

0
233

Tigray-newsbanner-cropRobemedia.com would like to say thank you! to the first Tigray born citizen solidarity message to stand with Oromo People when the Tigray fascist commit genocide on the Oromo People. We welcome your solidarity message and we hope you will stand with us to abolish the 21 century fascism in Ethiopia. It is unfortunate this current fascist cultivated in your society and attempt to colonize the rest of us in the name of Tigray people. Say “NO” to fascism!

ተደጋጋሚጭፍጨፋዎችእንዲቆሙአስጨፍጫፊዎች አስጨፍጫፊዎች አስጨፍጫፊዎችመወገድአለባቸው እኛምኦሮሞዎችነን ህወሓት/ኢህአዴግ ላንድ አራተኛ ምእተ ዓመት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ የጅምላና የተናጠል
ፋሽስታዊ ጭፍጨፋዎች እያካሄደ፣እያሰረ፣ እየደበደበ፣ የህዝባችንን ሰብኣዊ መብትና ነፃነት ረግጦ፤ በቋንቋ እየከፋፈለ፣ በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ፣ የህዝብ ሃብት እየዘረፈና በሙስና ተዘፍቆ ህዝባችንን አፍኖ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡

“ህወሓት/ኢህአዴግ” የሚል መጠሪያ ስንጠቀም፣ ከህወሓት በስተቀር ሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከህወሓት ነፃ የሆነ ድርጅታዊ ህልውና ኖሯቸው እንደማያውቅ፤ ህወሓት ሌሎቹን ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብን ተቆጣጥሮ መግዛትና ለመበዝበዝ የጠፈጠፋቸው ድርጅቶች መሆናቸውን ለመግለፅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ ኣባል ድርጅቶች በወታደራዊ የሃይል ልዩነት ላይ የተገነባ የይምሰል ጥምረት በስልጣን ክፍፍል ላይ የህወሓት የበላይነት አረጋግጧል፡፡ ህወሓት በሰራዊት፣ በደህንነት፣ በውጭ ጉዳይ፣ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የበላይነት ስልጣን፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ በኢኮኖሚና በቻይና የኢትዮጵያ የአምባሳደርነት ቦታ ሳይቀር ያለ ማቋረጥ መቆጣጠሩ፣ ህወሓትን ባለ ርስት እንዲመስል አድርጎታል፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈፀሙ ግፎች የህወሓት ባለስልጣኖች እንደ ስልጣናቸው ከፍተኛ ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሌሎቹ የኢህአዴግ ኣባል ድርጅቶች ባለስልጣኖችም ከመጠየቅ ሊድኑ አይችሉም፡፡
ህወሓት ባንድ በኩል የደርግ ኣገዛዝን ለማስወገድ ባስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች ህይወታቸውን የሰዉበት ድርጅት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሲመሰረት ጀምሮ የተቆጣጠሩት ግለ ሰቦች ፀረ ኢትዮጵያ ስለሆኑ ሌሎች አባላትን አግልለው የድርጅቱ ዓላማ የትግራይ ሬፐብሊክ መመስረት እንደሆነ በማኒፌስቶ ገልፀው ነበር፡፡ እነዚህ ግለ ሰቦች የመገንጠል ዓላማቸው ለመተው ቢገደዱም በኢትዮጵያ ደረጃ ስልጣን ከያዙ በሁዋላም ሉአላዊነትና በኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ጥያቄዎች ላይ የማይታመኑ መሆናቸውን ደጋግመው አሳይተዋል፡፡ በዚህ መሰረት በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ህወሓት ብሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ የሰጠ አገዛዝ የለም። አሁንም ህወሓት/ኢህአዴግ ግልፅነት በጎደለው አሰራር የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን የመስጠቱ አደጋ ስላለ የኢትዮጵያ ህዝብ ለያውቀውና ሊቃወመው ይገባል፡፡ egnam_oromowoch_nen

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here