How many times the disinformation minster lies? TPLF mouth mouthpiece, Getachew Rada

0
744
How many times the disinformation minster lies to the Ethiopia people? How many times he controlled the riot against TPLF fascism? you might ask? the answer would be he is lying indefinitely to hinder the fire against TPLF fascism. Who are the federal government anyways? the answer should be TPLF, the Tigray fascist group. They are the source of the problem. The TPLF instigate ethnic conflicts in Gambella and then subjugate the region under TPLF monopoly, we used to such tactic for years. See  the one instance of people resistance in Guji, Oromia this week and judge the disinformation mister yourself.  Here is the image of ordinary citizen  marched in thousands to resist TPLF fascism.

Happened this week in Guji, Oromia

guji2

“አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገሪቱ አንዳንድ ክልሎች ተነስተው የነበሩ ሁከቶችን መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ሙሉ በሙሉ ማርገቡን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

በኦሮሚያ እና አማራ እንዲሁም በጋምቤላ ክልል የተፈጠሩት ችግሮች መፈታታቸውን አቶ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል በተለይም በሶስት ዞኖች ህዝቡያነሳቸውን ትክክልኛ ጥያቄዎች አቅጣጫውን በማስቀየር የተፈጠረው ሁከት ሙሉ በሙሉ መክሰሙን አስረድተዋል።

ሁከቱ እንዲከስም ህዝቡ ያደረገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ጥቂት ወገኖች ያነገቡት ሴራ ግን ከሽፏል ብለዋል።

የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በህዝቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ እንዳይተገበር ሲወስን ከዚህ ጋር ተያይዞ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ አንዱ ግርግሩ ጠልፏቸው ያለ በቂ ግንዛቤ በሁከቱ ሲሳተፉ የታሰሩ አካላት ጉዳይ ተጣርቶ እንዲፈቱ የሚል አንዱ በመሆኑ፥ ይህ በክልሉ መንግስት እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።

ሆን ብለው የወንጀል ድርጊት ውስጥ በመሳተፍ የሰው ህይወትና ንብረት ያወደሙ አካላት ግን በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል።

በግርግሩ ህይወታቸውን ላጡ ግለሰቦች ቤተሰብ ካሳ ለመክፈል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል።

በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ ግለሰቦች የግርግር ድባብ ለመፍጠር የሚያስችሉ ሙከራዎች ይታያሉ ነገር ግን ድባቡ ከመሬት ላይ ይልቅ በማህበራዊ ትስሰር ድረ ገጾች ላይ ነው ብለዋል።

በአማራ ብሄረሰብና በቅማንት ማህበረሰብ መካከል በተመሳሳይ በጥቂት ወገኖች ተፈጥሮ የነበረው ግርግር ተወግዶ ዛሬ አከባቢው ወደ ሙሉ ሰላምና ወደ ተረጋጋ ህይወት መመለሱን አቶ ጌታቸው አንስተዋል።

በጋምቤላ ክልል በግለሰቦች መካከል የተፈጠረው ግጭት ወደ ብሄር ብጥብጥ ማምራቱ የክልሉ መንግስት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ባለመቻሉ የተከሰተ ነው ብለዋል።

የፖለቲካ አመራሩ መልካም አስተዳደርን የማስፈን ቁርጠኝነት መፈተሽ አለበት ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ፥ የዚህ ክፍተት የአኙዋክና የኑዌር ብሄረሰቦች ወደ ግጭት ማምራታቸውን አንስተዋል።

ይህ ወደ ክልሉ የፀጥታ ሃይል በማምራቱ በክልሉ መንግስት ጠያቂነት የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ የማረጋጋት ስራ መስራቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በተለይም የክልሉ የፀጥታ ሀይሎች፣ ልዩ ፖሊስ እና ሚሊሻ የመሳሰሉት ጎራ ለይተው ወደ ለየለት የብሄር መጠፋፋት የሚደርሱበት ምልክቶች በመታየታቸው የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል የፀጥታ ተቋማት በጉዳዩ ውስጥ ጣልቃ ገብተው የፀጥታ ሀይሉ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈቱ በማድረግ ወደ መከላከያ ካምፑ እንዲገቡ መደረጉንም ገልፀዋል።

በቀጣይ ግን በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ብሄረሰቦች መተማመንን እንዲፈጥሩ የማድረግ ስራ ይሰራልም ብለዋል።

የመሰረተ ልማቶችንና ሌሎች የልማት አውታሮችን መዘርጋትና፣ መልካም አስተዳደርን የማስፈን ቁርጠኝነትን በማከል ችግሩን የመቅረፍ ስራ ይሰራል ነው የተባለው።

መልካም አስተዳድር

መልካም አስተዳደር ለማስፈን ህዝቡን ያሳተፈ ስራ በየአከባቢው እየተሰራ ስለመሆኑ አቶ ጌታቸው አንስተዋል።

ችግር የፈጠሩ አካላት ላይ የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአማራ፣ አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያና በሌሎችም አከባቢዎች አርምጃ የመውሰድ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

እርምጃው የታችኛው የአስተዳደር አርከን ላይ ብቻ የታጠረ ይመስላል የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ሚኒስትሩ፥ ከህዝብ ጋር ስራ ሲሰራ ህዝቡ የሚያወቀው አገልግሎት የሚሰጡትን ነው፤ ለዚህም ነው እርምጃው ከታች የተጀመረው ብለዋል።

ህዝብን የሚያጉላላ እና ተገቢውን አገልግሎት የማይሰጥን የታችኛውን አመራር ስራውን እንዲቀጥል የሚንከባከብ ከፍተኛ የስራ አመራር ካለም በሂደት እሱም እርምጃው የሚወሰድበት ይሆናል ብለዋል።

የግብርና ምርቶች የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል?

ከድርቁ ጋር ተያይዞ የእህል ምርት የዋጋ ጭማሪ እንዳያሳይ መንግስት ሰፊ ስራ መስራቱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

መንግስት የእርዳታ እህል ብቻ ሳይሆን ገበያውን ለማረጋጋትም ሰፊ ግዢ የፈጸመ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የዋጋ ግሽበቱ እዚህ ግባ በሚባል ደረጃ እየጨመረ አይደለም ብለዋል።

ሆኖም ግን መንግስት የዋጋ ግሽበት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችሉ ተከታታይ እርምጃ መስወዱን እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ውጭ ምንዛሪ እጥረት
አቶ ጌታቸው ከውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ መቀረፉን ተናግረዋል።

በውጭ ምንዛሪ አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቀነስና የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ እየሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ህብረትን ከመንግስት ጋር የተጠናከረ ግንኙነት እንዳለው ያነሱት አቶ ጌታቸው፥ እንደውም በቅርቡ የ270 ሚሊየን ዩሮ የልማት ፓኬጅ ድጋፍ ማድረጉንም አንስተዋል።

ከአውሮፓ ካውንስል ጋርም መንግስት የተጠናከረ ትብብርና ግንኙነት አለው ሲሉም ሚኒስትሩ ይናገራሉ።

የአውሮፓ ፓርላማ ጥቂት አባላቶች ግን በአንዳንዶች እየተመሩ ሃገሪቷን ጥላሸት ለመቀባት መሯሯጣቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።

አና ጎሜዝ ደግሞ የዚህ የቡድኑ አስተባባሪ ሆነው ቢቀርቡም ያወጡት ሪፖርት በራሱ እርስ በራሱ የሚምታታ እንደሆነ ገልፀዋለ።

መንግስት በሪፖርት የተጠቀሱትን ግን አስቀድሞ ለራሱ ብሎ እየሰራቸው እንደሆነ አብራርተዋል።
የህዳሴው ግድብ

የህዳሴው ግደብን አስመልክቶ ሰሞኑን በሱዳን ካርቱም የተደረገው ውይይትም በግድቡ ላይ ጥናት ለማድረግ የተመረጡት ኩባንያዎች ያቀረቡትን ፕሮፖዛል አፅድቋል ብለዋል።

ነዳጅ ዋጋ መቀነስ

የነዳጅ ዋጋ መቀነስን አስመልክቶም የነዳጅ ግዢ በየእለቱ የሚፈፀም ባለመሆኑ በየጊዜው ዋጋው እንደማይከለስ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

መንግስት የነዳጅ ዋጋን የሚፈፅመው በ6 ወር አንዴ በመሆኑ የዋጋ ክለሳው ነዳጁ በተገዛበት ጊዜ በነበረበት የሚወሰን መሆኑንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

መንግስት የነዳጅ ዋጋ በቀነሰበት በአሁኑ ጊዜ የሚፈፅመው ግዢ ይኖራል ያሉት አቶ ጌታቸው፥ ይህም እንደ ገበያው ሁኔታ የዋጋ ቅናሽ ሊደረግበት እንደሚችል አስታውቀዋል።
በሞላልኝ ከሳቴብርሃን”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here