Konso people have been protesting over the last several months against land grab, demanding self-governing province and improvement in basic development

2
797

የኮንሶ ህዝብ የጀመረውን የአከላለል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በህዝቡ ላይ በደቡብ ልዩ ኃይልና መከላከያ ሰራዊት እየደረሰ ያለው የአፈና ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚሁ መሰረት በከተማው የሰፈረው ታጣቂ ከከተማዋ አጎራባች ቀበሌዎች እየዘመተ በህዝቡ የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት በሚል በዜጎች ላይ በሚወስደው የኃይል እርምጃ በ- ደቤና ቀበሌ ገ/ማ አቶ ‹‹ሷይታ ጋራ ›› ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ወጣት ‹‹ ተስፋዬ ማሙሽ›› ከ -ከርታሌ ቀበሌ እግሩ ተሰብሮ በባህል ህክምና እየተደረገለት በካራት ከተማ የሚገኝ ሲሆን አንድ የ65 ዓመት አዛውንትም ተሰብረው ባሻ ጤና ጣቢያ ይገኛሉ፡፡

ከባለፈው ዓርብ/25-06-08/ ጀምሮ 23 ሰዎች/ሃያ ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት/ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው በከተማዋ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡ በከተማዋ የሚገኙት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ የተዘጉ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛው ወደ እስር ቤት ተቀይሯል፡፡ ወደከተማው የሚያስገቡ መንገዶች እስካሁን የተዘጉ ሲሆን በተለይ የ -ደራ እና ጃርሶ ቀበሌ ነዋሪዎች መትረየስ በታጠቁ የልዩ ኃይል አባላት ተወረዋልአንድሁም በዛሬው እለት ድራይቴ ቀበሌ ጭምር በልዩ ሀይል እነደተከበበ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በጃርሶ ቀበሌ ሰገን ወንዝ ዳር የሰፈረው ኃይል የነዋሪዎችን ፍዬሎች እየዘረፈ አርዶ እንደሚበላ፣ የፓፓያ፣ማንጎ አቮካዶ እና የፍራፍሬ ዛፎችን በበቀል ስሜት እያበላሸ/እያወደመ እንደሚገኝም ህዝቡ በምሬት እየገለጸ ነው፡፡ ታጣቂ ኅይሉ በዚህ የኃይል እርምጃ የካራትን ከተማ አቋርጦ የሚያልፈውን የአርባ ምንጭ -ጂንካ መንገድ ማስከፈት ቢችልም ከተማዋን ከማሳለፍ ውጪ የሚሰጠው ዋስትና ያለመኖሩ አሽከሪካሪዎችን ስጋት ላይ በመጣሉ ከመንግስት መኪናዎች ውጪ የትራንስፓርት እንቅስቃሴ አይታይም፡፡

የመንግስት መኪና ተጠቃሚዎችም ቢሆኑ ከልዩ ኃይል ጋር ተነጋግረው መግባባት ባለመቻላቸው በትናንትናው ዕለት የደቡብ ኦሞ/ጂንካ ባለሥልጣናትን ይዞ ይጓዝ የነበረ መኪና ለ2 ሰዓታት ካራት ላይ በታጣቂ ኃሎች ታግቶ ቆይቶ እንደተለቀቀ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአጠቃላይ ከተማዋና አካባቢው በመኪና ላይ በተጠመዱና የነፍስ ወከፍ መትረየስ ታጣቂዎች ተወሮ፣ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ከዳር እስከ ዳር በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል ፡፡ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ፣ሴቶችና ህጻናት ሳይቀሩ ቱንም ዋጋ እንከፍላለን እንጂ ጥያቔኣችን ሳይመለስ ወደቤት አንገባም /አንመለስም በማለት ያላቸውን ቁርጠኝነት እየገለጹ መሆኑን እንዚሁ ታማኝ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ እኛም የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ሆይ ‹‹አፈና እና የኃይል እርምጃ ›› የህዝብን ብሶት ሲባብስ እንጂ ለህዝብ ጥያቄ መልስ አይሆንምና ከህዝቡ ላይ እጅህን አንሳ፣ ለሰላማዊ ጥያቄው ተገቢውን ምላሽ ስጠው፣ ህገ መንግስታዊ መብቱን አክብርለት እንላለን ፡፡
ድል ለምስክኗ ኮንሶ!!

2 COMMENTS

  1. “The Ethiopia constitution will end if the human right of people will not be solved.” god will return the freedom of konso know.

  2. i am a konso student so the inhuman action must be stopped and the question of the society must be answeard according to ethiopian conistitution!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here