Unknown secret of Ethiopian Airline

0
278

ለዘመናት የታፈነ ሀይለኛ ምስጥር
=====================
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉድና ለምን እንደሚሸጥ
(ET is in deep trouble too)
=====================
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምናልባትም በአለም ካሉት የኮርፖሬት ካምፓኒዎች ጥያቄ የጠየቁ ሰራተኞችን የሚቀጣበት የምድር እስርቤት ያለዉ ብቸኛዉ ካምፓኒ ሳያደርገዉ አይቀርም፡፡ በአየር መንገዱ አሰራር ላይ ጥያቄ ያነሳ ሰራተኛ በእቃ መጫኛ አንጋር አካባቢ ወደ ሚገኘዉ ቀዝቃዛ እስር ቤት ለሳምንታት ወይም ለወራት ልትታሰር ትችላለህ፡፡ሴቶች ከሆኑ ደግሞ በዚህ እስር ቤት ጠባቂዎች የመደፈር ጉዳይ አለ፡፡ብዙ ሰዉ ይህ ድርጅት አትራፊ ነዉ ለምን ይሸጣል ይላል፡፡ በርግጥ በአመት 50 ወይም 100 እስከ 200 ሚሊየን ዶላር አትርፎ ያዉቃል፡፡ነገር ግን ከአሜሪካ ባንኮች፤ ከቻይና አግዚም ባንክና እና ከህንድ ባንክ የተበደረዉ ብድር የትእየለሌ ነዉ፡፡ ለራሱ ለድርጅቱ ብቻ ሳይሆን መንግስት በዚህ ድርጅት ሰበብ ለራሱ ይበደርበታል፡፡ አሁን ላይ በየአመቱ መንግስት ከሚከፍለዉ የብድር እዳ 60% የአየር መንገዱን እዳ ይሸፍናል፡፡እስኪ ከብዙ ችግሮች ዉስጥ አንዱን ለምሳሌ ላንሳዉ፡፡

የአምስቱ የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ Boeing 787 Dreamliner አውሮፕላኖች የማኔጅመንቱ ድብቅ ቁማር ANA (All Nippon Airways) በመባል የሚታወቀው የጃፖኑ አየር መንገድ ከቦይንግ ካዘዛቸው በርካታ ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ውስጥ ቀድመው ተመርተው የነበሩት B787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች በነበራቸው የምርት ጥራት ችግር የዲዛይን ደረጃቸውን ስለማያሞሉ እና በዚሁም ምክንያት አውሮፕላኖቹ ምንም ሳይጭኑ ከባድ በመሆናቸው እና የጭነት መጠናቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ የነዳጅ ፍጆታቸው ከፍተኛ በመሆኑ እና አጭር ርቀት ብቻ መብረር በመቻላቸው በመሳሰሉ ትክክለኛ ምክንያቶች ከቦይንግ አልወስድም ብሎ ስለተዋቸው ፈላጊ አተው ለበርካታ አመታት ቆመው ነበር።የኢት ማኔጅመንት ግን እኒህን 5 አዉሮፕላኖች በጥቅም ተደልሎ ተቀብሏቸዋል፡፡

በቦይንግ አሰራር መሰረት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለአየር መንገዶች ብቻ እንደሚሸጥ ይታወቃል። በዚህም መሰረት South America አካባቢ የሚገኝ አውሮፕላን ገዝቶ በማከራየት የሚታወቅ አንድ ካምፖኒ እነዚህን አውሮፕላኖች ከመግዛቱ በፊት በዚህ standard ማንም እንደማይከራየው ስለሚያውቅ እና በቀጥታ ቦይንግ ስለማይሸጥለት በድርድር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያንዳንዱን 90 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ከቦይንግ እንዲገዛው ካደረገ በሆላ ይሄው ካምፖኒ ገንዘብ ጨምሮ ወደ 120 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መልሶ በመግዛት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ25 አመታት በላይ አውሮፕላኑ እስኪያረጅ ድረስ ተከራይቶ እንዲያበርለት የሚያስገድድ ውል ከማኔጅመንቱ ጋር ይፈራረማል፡፡ይሄው ዛሬም ተዋረዱ ሲላቸው ከጅምሩ ጀምሮ በፋን ብሌድ ዝገት፣ በሞተር ዘይት መፍሰስ በመሳሰሉ አወዛጋቢ ችግሮች ሲገጥመው በቆየው የተገጠመለት Rolls-Royce Trent 1000 ሞተር ችግር ምክንያት ፓርቱ እስኪገኝ ድረስ አራቱ አውሮፕላኖች እዳቸው እየተከፈለ ላልታወቀ ረጅም ጊዜ እንዳይበሩ ተደርገዋል። የዚህ አውሮፕላን የሊዝ ክፍያ በዶላር በወር 800,000 እስከ 1.25 ሚሊየን USD ድረስ ነው (በዚህች በደሀ ሀገር ላይ ይሄ ዶላር ምን ያህል ቁም ነገር ሊሰራ እንደሚችል ማሰብ ነው) ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሌሎቹ B787 ድሪም ላይነሮች የነዚህ የተበላሹ አውሮፕላኖች መስመርን ለመሸፈን ሲባል ለጥገና መግባት ከነበረባቸው ሰአት በላይ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here